ባሕረ ሓሳብ STORE ወሳኝ ዚና You-tube ABOUT CONTACT
ባሕረ ሓሳብ STORE ወሳኝ ዚና
ሀሳበ ባሕር (የዘመን ቁጥር)
ጊዜን መቁጠር ዘመንን መስፈር የተጀመረው ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ ነው፡፤ እግዚአብሔር አምላክ አዳምንና ሄዋንን ፈጥሮ በነፍስ ሕያዋን አድርጎ በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ ከአንዲት እፀ በለስ በቀር ከፀሐይ በታች ከምድር በላይ ባለው ሁሉ ላይ አሰልጥኖ ( ሾሞ) በገነት አኖራቸው፡፡ ሁለቱ የመጀመሪያ ሰዎች አክብረው ለሰባት ዓመት በገነተ ያለምንም ችግር ሕጉን ጠብቀው ትእዛዙን ኖረዋል፡፡ “ በመጀመሪያው ሱባኤ፣ በመጀመሪያው ኢዮቤልዩ አዳምና ሚስቱ በገነት ” ኖሩ ይላል፡፡ ኩፋ 4÷14 ከዚህ በኋላ አዳም በጠላት ዲያብሎስ ክፉ ምክር ተታሎ ሕጉን ጥሶ፣ ትእዛዙን አፍርሶ ከተሳሳተ በኋላ ከገነት ተባረረ፡፡ እግዚአብሔርም በዚያው እንደተባረረ እንዲቀር ስላልፈለገ በ5500 ዘመን ሰው ሆኜ አድንሀለሁ ወደ ቀደመ ክብርህ እመልስሃለሁ ብሎ ተስፋ ሰጠው፡፡ አዳምም ይህን ተስፋውን ይዞ ለልጆቹ ፣ልጆቹም ለልጅልጆቻቸው ነገሩአቸው ፡፡ እነሱም ከአባቶቻቸው ተቀብለው እኩሎቹ በፀሐይ፣ እኩሎቹ በጨረቃ፣ ሌሎቹም በከዋክብት እየቆጠሩ መኖር ጀመሩ፡፡ በዚህ ሁኔታ የዘመን አቆጣጠር ታሪክ ተጀመረ፡፡
የዘመን አቆጣጠር ታሪክ መነሻ የ5500 ዘመን መፈጸምን ለመድረስ የሚደረግ ወደ ታች የሚቆጠር ሂደት ነበር፡፡ ከአዳም ጀምሮ በዚህ ሁኔታ ቢነሳም በዚሁ አልቀጠለም;፡፡ ምክንያቱም የሰው ዘር በምድር ላይ እየበዛ በሄደ ቁጥር ለቀን፣ መቁጠሪያ ለዘመን መስፈሪያ፣ ለሰው ልጆች መገልገያ ሊሆኑ የተፈጠሩ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብትን የሰው ልጆች አምላካቸው አድርገው አመለኳቸው፡፡ ነገር ግን ተስፋቸውን ያልረሱ ጥቂት ሕዝቦች ብቻ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ቀሩ፡፡ ስለሆነም የዘምን አቆጣጠር በልዩ ልዩ ሕዝቦች በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አካሄዶችን በመከተል ሲሰራበት ኖሯል፡፡
በመሆኑም ከአዳም እስከ ልደተ ክርስቶስ ያለውን የዘመን አቆጣጠር ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

|
Share to
• Lorem ipsum dolor sit amet
• Consectetur adipiscing elit • Lorem ipsum dolor sit amet • Consectetur adipiscing elit |
Awards• Lorem ipsum dolor sit amet
• Consectetur adipiscing elit • Lorem ipsum dolor sit amet • Consectetur adipiscing elit |
Publications• Lorem ipsum dolor sit amet
• Consectetur adipiscing elit • Lorem ipsum dolor sit amet • Consectetur adipiscing elit |
Interviews• Lorem ipsum dolor sit amet