salary application .............
የክርስቶስ ልደት ታህሳስ 29 ወይስ ዴሴምበር 25?
የእኛ ቤተ ክርስቲያን ልደትን ለምን ታኅሣሥ 29(28) ቀን ታከብራለች? ምዕራባውያንስ የልደትን በዓል ለምን December 25
ያከብራሉ? የጌታችን በዓለ ልደት መቼ ተጀመረ? መድኃኒታችን የተወለደበት ቀን ይታወቃልን? የልደት በዓል የሚከበርበትስ ቀን
በምዕራባውያንና በእኛ ቤተ ክርስቲያን ለምን ተለያየ?
የእኛ ቤተ ክርስቲያን ልደትን ለምን ታኅሣሥ 29(28) ቀን ታከብራለች? ምዕራባውያንስ የልደትን በዓል ለምን December 25
ያከብራሉ? የጌታችን በዓለ ልደት መቼ ተጀመረ? መድኃኒታችን የተወለደበት ቀን ይታወቃልን? የልደት በዓል የሚከበርበትስ ቀን
በምዕራባውያንና በእኛ ቤተ ክርስቲያን ለምን ተለያየ?
ታህሳስ 22 ቀን
|
ይህ እለት በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ብስራተ ገብርኤል ይባላል፤ ይህም ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታንእንደምትወልድ ብስራቱን የነገረበት ቀን ብላ አስባው ትውላለች።መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብስራቱን የነገራት መጋቢት 29 ቀን በዕለተ እሁድ ከቀኑ ሦስት ሰዓት ላይ ነው፡ ታዲያ ታህሳስ 22 ቀን ለምን እናከብረዋለን ካሉ ምክንያቱ እንዲህ ነው፤ ምንግዜም ወርኃ መጋቢት ታላቁ ዓቢይ ጾም የሚውልበት ወር ነው። በዚህ በዓቢይ ጾም ደግሞ ሐዘን፤ ለቅሶ፤ ጾም፤ ጸሎት እንጂ ደስታ፤ ፌሽታ፣እልልታ፤ ጭብጨባ የለም ፍጹም የሐዘን ወራት ነው ። ለዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን እንደዚህ ዓይነት ስርዓት ሰሩ: የመጋቢት 27 ስቅለቱን ጥቅምት 27 ቀን እንዲሁም የመጋቢት 5 አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍትቀን ወደ ጥቅምት 5 ቀን ዞሮ እንዲከበር አደረጉ፡፡ የመጋቢት 29 ብስራቱን ደግሞ ወደ ታህሳስ 22 ቀን ዞሮ የጌታን ልደት ከመከበሩ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ብስራቱ መከበር አለበት ብለው የሰሩትን ስርአት ቤተክርስቲያን ተቀብላ ይኸው ዛሬም ድረስ ታከብረዋለች ፡፡" አብሳሪ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እጅግ አጽናኝና አስደሳች የሆነውን ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛምእግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈጸም ደስ ይምንልበትን ጸጋ አሰጠን።የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ፀሎት ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ከሁላችን ጋር ጸንቶ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። |